Thursday, March 17, 2016

“ይቅርታ” ወይም “ሰላም”ሃይለማርያም ደሳለኝ ባለፈው ሳምንት ያደረጉት ቃለመጠይቅ አነጋጋሪ ነበር። ከኦሮሞ ህዝብ አመፅ ጋር በተያያዘ የሰነበተውን ችግር ሌላ አካል ላይ ማላከክ እንደማይገባ መናገራቸው ከኢህአዴግ ጠባይ አንፃር ያልተለመደ ነበር። በውስጥ ባለ ችግር ምክንያት የህዝብ ጥያቄዎች ፈጣን ምላሽ ባለማግኘታቸው ህዝብና መንግስት ተቃቅረው ጉዳዩ ወደ ግጭት ደረጃ መድረሱን ማመናቸው አንድ እርምጃ ወደፊት ነው። ችግሩ የመልካም አስተዳደር እጦት መሆኑን መግለፅ መቻላቸው ይደነቃል። ሃይለማርያም በዚህ ደረጃ ችግሩን አምነውና ተቀብለው ሲያበቁ፤ በመጨረሻ ለተፈጠረው ችግር በጥቅሉ ህዝብን ይቅርታ ጠይቀዋል። ይቅርታ ጥየቃው ካንገት በላይ ነው ወይስ ካንገት በታች ለጊዜው ባናውቅም፤ ይቅርታ መጠየቅ በራሱ ስልጣኔ ነው።

Wednesday, March 9, 2016

ፍርሃትም ይሸነፋል

       ዝነኛው አሸማጋይ ፕሮፌሰር ይስሃቅ ኤፍሬም መሰንበቻውን ስራ እንደበዛባቸው ተሰምቷል። የኦሮሞን ህዝብ አመፅና ጥያቄ በሰላም ለመጨረስ እዚህም እዚያም እየደዋወሉ ልብ የሚነኩ እግዚአብሄራዊ ቃላት ተናግረዋል። የፕሮፌሰሩ ጥረት በደፈናው የሚነቀፍ ባይሆንም አይሳካላቸውም። የሽማግሌው የእርቅ መንገድ ጥሎ ማለፍ ይዘት እንዳለው ካለፈ ድርጊታቸው ትምህርት ተገኝቷል። በተጨማሪ ድርድር ወይም እርቅ ሲታሰብ መላ የኢትዮጵያን ህዝብ የመብት ጥያቄዎች ታሳቢ በማድረግ እንጂ፤ ጉልበት ካገኘው  ሃይል ጋር ብቻ የመደራደር ዝንባሌ ያለፈውን ስህተት መድገም ይሆናል። በመሰረቱ ወያኔ በስውር ሽማግሌ መላክ መጀመሩ ጊዜ ለመግዛት ካልሆነ ከልብ እርቅና መደራደር ፈልጎ እንደማይሆን ይገመታል። ከፋፍሎ የማዳከም የህወሃት አካሄድ ገና ድሮ ተባኖበታል።

Friday, February 19, 2016

ከመባለግ መሳሳት ይሻላል

ሃይሌ ገብረስላሴ ላይ ሰሞኑን በወረደበት ድብደባ በጣም ተገርሜያለሁ። ሃይሌ የፖለቲካ ሰው አይደለም። የተናገረው የአፍ ወለምታም ሊሆን ይችላል። በፖለቲካው በኩል ተፅእኖ የማድረግ ችሎታውም ያን ያህል አይደለም። ምንድነው ይሄ ሁሉ ጩኸት? ደግሞስ ምን ስህተት ተናገረ?

ከኦሮሞ ማዕበል ማግስት …

        በአለማችን ላይ ወጣቶች በአንድ ልብ የተሳተፉበት ያልተሳካ የአብዮት ታሪክ አናውቅም። የጊዜ ጉዳይ ብቻ ነው። ይህችን እየፃፍኩ ሳለ የማያቋርጥ፣ የተቀናጀ የአመፅ ዜና ከኢትዮ - ኦሮሚያ እየሰማሁ ነበር። ዝምታው ማብቃቱ ግልፅ ነበር። የኦሮሚያ ወጣቶች የስርአቱን ታጣቂ ሃይል በጦርና በጠመንጃ ይፋለሙት ይዘዋል። ከሻሸመኔ ወደ አዲስአበባ መንገድ ተዘግቶአል። ልማደኛዋ ኮፈሌ ጦርሜዳ ሆናለች። ብረት ለበስ ጦር ኮፈሌና ሻሸመኔ ገብቷል። በጥቅሉ ወለጋና ሃረርጌ ፀጥታ የለም። ሱሉልታ ብሶበታል። ጭራሽ ገበሬዎቹ ያስለቀቁትን መሬት መከፋፈል ጀምረዋል። ደራ ነፃ ነው።

Wednesday, February 17, 2016

የበዕውቀቱ ስዩም ወጎች

          በዕውቀቱ ስዩም “ከአሜን ባሻገር” በሚል ርእስ ያሳተመውን መፅሃፍ አነበብኩት። እንደተለመደው ጥሩ ተራኪ ነው። በዚህ ባዲሱ መፅሃፉ በዕውቀቱ ስለማንነቱ ያሰፈረው አዲስ መረጃ ግን ቀደምት ስራዎቹን ወደ ሁዋላ ተመልሼ እንዳገላብጥ አስገድዶኛል። በዕውቀቱ ባለተሰጥኦ ነው። ተፈጥሮ ብእረኛነትን ያለስስት ያስታቀፈችው ድንቅ የዘመናችን ገጣሚ ነው። በተለይ በአጫጭር ስነግጥሞቹ የሚያነሳቸው ጭብጦች አስደማሚ ስለመሆናቸው ብዙ ተነግሮለታል። ለአብነት ሙስናን በአምስት መስመሮች ብቻ የገለፀበት መንገድ የቅኔ ችሎታውን ፍንትው አድርጎ ያሳያል፣